የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም

"እኔ ይህን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ከአድዋ ዘመቻ እና ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ለይቼ አላየውም" ክቡር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትር የማህበራዊ ጉዳዬች አማካሪ ሚኒስትር +++++++++++++++++++++++++ አዲስ አበባ ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የተጀመረውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ከአድዋ ዘመቻ እና ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ለይተው እንደማያዩት ክቡር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትር የማህበራዊ ጉዳዬች አማካሪ ሚኒስትር ገለፁ። ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመንግስት አስተዳደር ፖሊሲ ፣ የሪፎርም የትግበራ ምዕራፍ ላይ መሆኑን ገልፀው በዚህ ረገድ ቀጣይ የሚሰሩ ሥራዎች በተለይ የሚዲያና የኮሚሙኒኬሽን ሚናው ምን መሆን እንደሚገባው አብራርተዋል። አገልግሎትን ስናስብ የኛ ህብረተሰብ መንግስት ማለት በታችኛው የመንግስት መዋቅር ሥር የአገልግሎት መስኮት ላይ የተቀመጠውን ሰራተኛ እሱን ነው ብሎ እንደሚያስብ ተናግረዋል። በዚህ ሲቪል ሰርቫንት አማካኝነት ለተገልጋዩ በሚሰጠው በጎ ያልሆነ ምላሽ የሚወቀሰው መንግስት መሆኑን ነው ሚኒስትሩ ያነሱት። የቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት ሆነ ሌሎች ጉዳዩችን ለመከወን በዚህ ዘመን የመንግስት መስሪያ ቤት ጎራ ካሉ ያለ እጅ መንሻ ጉዳዩን ለመፈፀም አስቸጋሪ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ እና አንዳንድ ቦታ በጭራሽ አንደማይታሰብ ገልፀዋል። አገልግሎቱን በበቂ ሁኔታ ካላገኝ ተገልጋዩም የሚወቅሰው መንግስትን ነው ምንም ብትሰራለት ትልልቅ ህንፃዎች ብትገነባለት ለሱ ግድ የለውም እዛ ጋር አገልግሎቱን በበቂ ሁኔታ አላገኝምና እንግልት ደርሶበታል ከዚህ ችግር እንዴት አብረን ተባብረን እንውጣ እያለን ነው መንግስት ብለዋል። ተገልጋዩ ምናልባትም የሱ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ምንም ነገር ባይይኖርም በደረሰበት እንግልት መግስትን መውቀሱ እንደማይቀር ነው የተናገሩት። የአብዛኛው ሰው የኑሮ ሁኔታ ድግግሞሽ የበዛባቸው አገልግሎቶች ጋር የተያያዘ ነው ከአጠገቡ ካለው አገልግሎት መስጫ ተቋም /ሰው/ ጋር የሚያገናኝው በርካታ ጉዳዬች ይኖሩታል። ማንኛውም ፖርቲም በለው ድርጅት ግለሰብ ያለ ሲቪል ሰርቪሱ የአገልግሎት መሻሻል ዋጋ የለውም የትም ሁን የትም የማይነካው የህብረተሰብ ክፍል የለም ከታች ጀምሮ እስከ ላይ በዚህ መግስታዊ መዋቅር ውስጥ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እንደሚነካ ገልፀዋል። ዋናው ጥያቄ አሁን ከዚህ ችግር እንዴት እንውጣ ነው።መንግስት በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ሰፊ ግዙፍ ሪፎርም እየሰራ እደሚገኝ በዚህ ስልጠና እንደተገነዘባችሁ አውቃለሁ ብለዋል። ስለዚህ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባርና ኃላፊነቱን እንደ ዜጋ ሪፎርሙን ተረድቶ የሚከውነውን መከወን እንዳለበት አሳስበዋል። እንደ ዜጋ ሊበቃን ይገባል ይህ ጉዳይ የዜግነት ግዴታዬ ነው ከዚህ ችግር አባቴን ፣ እናቴን፣ እህቴን ፣ ወንድሜን ማውጣት አለብኝ የኔ ግዴታ ወይ የኔ እስተዋፅኦ ምድነው በዚህ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ብለን መነሳት አለብን ብላዋል። አክለውም የግድ ህዝባችንን ከዚህ ችግር ማውጣት አለብን እኔ የበኩሌን እንደ አንድ ዜጋ ባለኝ እውቀት እየሰራሁ ሪፎርሙን እደደገፍኩ እገኛለሁ። እናተም ሁላችንም ይህን በቅንነት አይተን መለወጥ መቀየር አለብን ብለዋል። የትም የመግስት መስሪያ ቤት ሰንገባ ተደስተን ጉዳያችንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፈፅመን መሄድ የምንችልበት ሁኔታ ይፈጠራል ለዚህ በርትተን ተግተን እሰራለን ብለዋል። በመጨረሻም ተሳታፊዎች ስልጠናው መዘጋጀቱ እጅግ በጣም እንደተደሰቱ እና በዚህ ሪፎርም የበኩላቸውን ድርሻ እደሚወጡ ተናግረው አገልጋይ ተርታ ላይ ብመደብም እንደ ዜጋ እኔም ተገልጋይ ሆኜ ተንገላትቻለሁ። እየተንገላታሁም ነው። ስለዚህ ይህንን ሪፍርም በጣም እፈልገዋለሁ። የቻልኩትንም ያህል እሰራለሁ። ሪፎርሙ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ከተባበርን ይሳካል።ጥቂቶች ብዙሀንን እንዲያገላቱ መፍቀድ ወንጀልም ሀጢአትም ነው።ሲቪል ሰርቪሶች በርቱ ብለዋል።

Share this Post