ትግበራ ምዕራፍ
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የሽግግር ምዕራፍ አጠናቆ ወደ ትግበራ ምዕራፍ እንደሚሻገር ገለፀ ።
”ሰው ገንዘብ ብቻ የሚያሳድድ ከሆነ የሆነ ጊዜ ችግር ውስጥ መግባቱ አይቀርም”
”እኔ ጠረጵዛ ላይ ሳልመራው የሚያድር አንድም ደብዳቤ አይኖርም። በየትኛውም ሰዓት ቢሆን በቀረበበት እለት ይመራል” የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
አዲስ አባባ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በተያዘው ሪፎርም ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሽግግር ምዕራፍ አጠናቆ ወደ ትግበራ ምዕራፍ እንደሚሻገር በአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ከሰኔ 27-29 ቀን 2017 ዓ.ም ለሠራተኞቹ ባደገረው የሽግግር ስልጠና አስታውቋል፡፡
በስልጠናው ላይ የፊዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) እንደተናገሩት አጠቃላይ ሲቪል ሰርቩሱ ያለበትን ሁኔታን ተረድቶ አዲሱ አመራር ከመጣ ጀምሮ አጠቃላይ የመንግስት አገልግሎት ዘርፉን ለመለወጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም ውጤት እየታየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዛሬ የምናካሄደው ሥልጠና ከሌላው ጊዜ የተለየ ታሪካዊ እና ትልቅ ፋየዳ ያለው ስልጠና ልንለው እንችላለን ።ተቋሙ ከዚህ በፊት ያሉበትን ችግሮች ቀርፎ በለውጡ ጎዳና ላይ በመሆኑ በሪፎርሙ የመጀመሪያው ዌቪ የሽግግር ምዕራፍ ከገቡት ስምንት ተቋማት መካከል አራቱ ተቋማት የሽግግር ምዕራፉን በቀረበው የምዘና መስፈርት ስላሟሉ ወደ ተግባር ምእራፍ የተሸጋገሩ በመሆኑ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም ከአራቱ አንዱ ሆኖ ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡
ከዥግጅት ምዕራፍ ወደ ተግባር ምዕራፍ ስለገባን ከወትሮ የተለየ ርብርብ ያስፈልገናል። ይህ ተቋም ሁለት ሥራ እና ኃላፊነት ነው ያለበት። አንዱ ራሱን መለወጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሌላው እዲለወጥ እና አርአያ መሆን ነው። ይህ ሪፎርም ለየት የሚያደርገው ሰርቶ ማሳየት እንጂ በመናገር ብቻ የሚፈፀም አይደለም። መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ፣የሲቪል ሰርቪሱ የሚመራበት ፖሊሲ ፣ ፍኖተ ካርታ ወዘተ --ሥራዎች ተጠናቀው ወደ ተግባር ገብተዋል። እንዲሁም የመንግስት ሰራተኛ አዋጁን አሻሽለናል፣ ስትራቴጂዎች፣ ማንዋሎች፣ መመሪያዎች ፣ደንቦች እና የህግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውን አብራርተዋል፡፡
እያንዳንዱ ሰው የተሰጠውን በአግባቡ ከሰራ ውጤታማ እንደሚኮን እና ለዚህም ራስን ማሸነፍ የመጀመሪያው መርሆችን መሆን አለበት ።ሪፎርሙ የግድ መሳካት ስላለበት የሚወሰደው እርምጃ ይኖራል የአገር ጉዳይ ከምንም ነገር በላይ ይበልጣልና ።ሰራተኛው እራሱን መጠበቅ : መታመን መስራት ይጠበቅበታል።ሰራተኛው ከፊት ለፊቱ ይህ እንደሚኖር ማወቅ አለበት። በየተሰማራንበት ሥራ ሁላችንም ትልቅ ኃላፊነት አለብን ።መሥራት እንችላለን ይህን ደግሞ በሥራችን አሳይተናል። ስለዚህ ወደ ኃላ የለም ።መስራት አሁንም መስራት የግድ መለወጥ ስላለብን ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡
አክለውም 10ኛውን የአፍሪካ ፐብሊክ ሰርቪስ ቀን አዘጋጅተን ከአንድ እስከ ሦስት የወጡት እኛ ሳንሆን ሌሎች የአፍሪካ አገራት ናቸው። በአፍሪካ ወደ ኃላ የቀረን መሆኑን መረዳት አለብን ።እውነት እውነቱን እንነጋገር የሆነ እንደምንዘፍነው ዘፈን አይደለም ።ወደ ኋላ ቀርተናል ይህን ማወቅ መረዳት ይገባናል ብለዋል፡፡
ሰራተኛው ይህን አውቆ ከእያንዳንዱ ሠራተኛ የሚጠበቀው ቅንነት ብቻ ነው። ትንሽ ነገር ነው የተጠየቃችሁት ።ከሁላችንም ከዚህ ስንመለስ ትንሽ:ትንሽ ነገር እንኳን ብንሰራ በድምሩ የሆነ ታእምር /Miracle/ ነው መፍጠር የሚቻለው።በዚህ መሰረት የሚሰራው ይበረታታል። የማይሰራው ይጠየቃል፡፡
እኛ እዚህ መድረክ ላይ የምንናገረውን ሁሉ እናደርጋለን ።በበጀት በኩል የሚያጋጥመን ችግር ብዙም ይኖራል ብለን አናስብም። ከመንግስት እና ከአለም ባንክ ድጋፍ ይደረግልናል። የሚጠበቅብን መከወን ብቻ ነው ።እኔ ጠረጵዛ ላይ ሳልመራው የሚያድር አንድም ደብዳቤ አይኖርም።እንደምታውቁት የቀረቡ ጉዳዬች በተቻለ መጠን ማታም ይሁን ጠዋት ወዲያው ነው መልስ የሚሰጠው ።እናንተም በስራችሁ እንዲህ ነው መሆን ያለባችሁ ። በጋራ ከሰራን ትልቅ ቱሩፋት ይኖረናል።ሁሌም ገንዘብ ብቻ የምታሳድድ ከሆነ የሆነ ጊዜ ችግር ውስጥ መግባትህ አይቀርም ። ሥራን አሳድ ከዛም ሥራው እራሱ ገንዘብ ይዞ ይመጣል ።የመጣውም ገዘብና ሀብት ዘላቂ ይሆናል። ካልሆነ ጠፊ ነው።እመኑኝ ይህ ነው የህይወት ልምዴ መስራት ጥሩ ነገር ነው ብለዋል፡፡
ስልጠናው ለሦስት ተከታተይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን በርካታ ዕውቀትና ትምህርት እንዳገኙበት በተደረገላቸው አጠቃላይ የሥልጠና መርሀ ግብር አንደተደሰቱ ሰራተኞቹ ገልፀዋል፡፡