በመትከል ማንሰራራት

አዲስ አበባ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሃግብር የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አከናውኗል። ****,****************,*******,*** የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን 7ኛ አመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ችግኝ ተከላ በለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 5 በተዘጋጀለት ቦታ አረንጓዴ አሻራ ለትውልድ አኑሯል። በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ይህን በአገር :በአፍሪካና በአለም አቀፍ ደረጃ ሊታሰብና ሊጠቅም የሚችል በክብር ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢንሼቲቪ በየአመቱ የሚከወን ታላቅ ተግባር መሆኑን ኮሚሽነሩ አውስተዋል። ችግኙ የተተከለበት ቦታንም በቅርብ ክትትል አልምተን ምቹ መናፈሻ ሰርተን ነዋሪዎች የሚናፈሱበት የሚገለገሉበት እናደርጋለን። ይህንንም እስከ ታህሳስ ወር ሰርተን ጨርሰን እናስረክባለን ብለዋል ። ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

Share this Post