የተቀናጀ ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ፕሮጀክት

{jcomments on}የፕሮጀክቱ አጭር ታሪክ

 1.   የፕሮጀክቱ መነሻ እሳቤ
 • የተቀናጀ ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ፕሮጀክት ያስፈለገበት ማዕከላዊ ጉዳይ ልማዳዊ የሆነውን የመረጃ አያያዝና በዚህም ላይ በመመስረት ያለውን ኋላቀር የአገልግሎት አሰጣጥ ዘይቤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ የመረጃ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ በመፍጠር በአገልግሎት አሰጣጥ መሰረታዊ የሚባል ለውጥ እውን ማድረግ ነው።
 • በልማዳዊው አሰራር የተለዩ ችግሮች፤ ልማዳዊው አሰራር በአንድ በኩል ከአሰራር ብቃትና ውጤታማነት ደካማነት፣ በሌላ በኩል ከሚጠይቀው ከትፈኛ የሃብት መጠን አንፃር የፈጠረው ሸክም በቀላሉ የሚገለጽ አይሆንም። ከዚህ ረገድ የሚከተሉት ተጠቃሽ የልማዳዊው አሰራር ዳካማ ጎኖች ናቸው፦
 • አገልግሎት ጥያቄና አሰጣጥ በአካል መደረጉ የሚፈጥረው የተለያየ ሃብት ወጪና የብቃትና ውጤታማነት ዝቅተኛነት፣
 • መረጃና ሰነዶች በመነካካታቸው ለጉዳት መጋለጣቸው፣
 • ፋይሎችን ከቦታ ወደ ቦታ ማንቀሳቀስ ያለው ውስብስብነት እንዲሁም አንድን መረጃ በአንድ ጊዜ መጠቀም የሚችለው አንድ ግለሰብ ብቻ መሆኑ፣
 • የድርጅትና የግለሰብ የግል መረጃ አጠባበቅ አስተማማኝነቱ ዝቅተኛ መሆኑ፣
 • በአደጋ መረጃ ቢጠፋ መጠባበቂያ ስለማይኖር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው መረጃዎች ጭምር ደብዛቸው ለመጥፋት የተጋለጡ መሆኑ፣
 • መረጃን ማስቀመጥ ከፍተኛ የቦታና የገንዘብ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ፣
 • ያለውን /የሲቪል ሰራተኛ/ መረጃ ለመከታተል አለመፍቀዱ/አለመቻሉ።
 • በአኳያው የሚዘረጋውና ስራ ላይ የሚውለው አዲሱ አሰራር ልማዳዊው አሰራር ያሉበትን ህጸጾች በማስወገድ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ ይኖረዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ ብቃትና ውጤታማነትን ከማምጣት ባሻገር፤ የአሰራር ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የማይናቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
 1. ቅድመ-ፕሮጀክት የተከናወነ ጥናት
 • የኢ.ስ.ሚ.ስ. ፕሮጀክት ተቀርጾና ጸድቆ ወደ ስራ ከመግባቱ ቀደም ሲል ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የመጠቀምን ፋይዳና አሰራር የመፈተሽ ሂደት ነበረ። በዚህ መልክ የተከናወኑ ተግባራት ፕሮጀክት ቀርጾ መዘርጋት አስፈላጊነት ያሳዩ ሁኔታዎችን በመፍጠር ፕሮጀክት መቅረጽ በሂደት መልክ እየያዘ እንዲመጣ አደረገ። የተከናወኑ ስራዎች ለዚህ ማሳያ ማድረግ ይቻላል።
 • በ1993 ዓ.ም. /ካሮስ የኮምፒውተር አገልግልት/ የኮምፒውተራዝድ ሲስተም ፍተሻ እንዲያካሄድ በተገባ ስምምነት የሚከተሉት ክፍሎች ተለይተውና የጊዜ ሰለዴ ተቀምጦ ፍተሻው ተከናውኗል፤ ሪከርድና ማህደር አገልግሎት፣ የስምሪት መምሪያ፣ የአደረጃጀትና ስራ ምደባ መምሪያ፣የኢንስፔክችን መምርያ እና የአስተዳደር ፍርድ ቤት።
 • በ1995 ዓም በተጻፉ የውስጥ ደብዳቤዎች ተጠንቶ ኮሚሽኑ መረከቡን፣ የተረከበውን አዲስ ሲስተም በስራ እንዲፈትሹ፣ ስራ ላይ እንዲውል፤ የታዩ ክፍተቶች ደግሞ ለአልሚው አካል ቀርበው እልባት እንደሚደረግባቸው ታይቷል።
 1. ኢ.ስ.ሚ.ስ. ፕሮጀክት መጀመር
 • ፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መስከረም 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ከአገር በቀል ኩባንያ ጋር በገባው ውል የአገሪቱን የሲቪል ሰርቪስ የሰው ሃብት መረጃ ቋት ለመያዝ ያሚያስችለውን የሲቪል ሰርቪስ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም /Integrated Civil Service Management Information System/ በይፋ ጀመረ። በዚያም መሰረት አዲሱን አሰራር ለመዘርጋት ወደ ስራ ገብቷል። ከስራው ስፋት አንጻር በምዕራፍ ተከፋፍሎ እንዲከናወን አቅጣጫም ተቀምጧል።
 • ህዳር ወር 2005 ዓ.ም. ፕሮጀክቱ ላይ በሙከራ ደረጃ ሊሳተፉ የሚችሉ የፌዴራልና የክልል ሲቪል ሰርቪስ መ/ቤቶችን  መርጠው እንዲያሳውቁ በመጠየቅ አዲሱን አሰራር በፍተሻ ደረጃ የመዘርጋትና ስራ ላይ ማዋል ተጀመረ።
 • የፕሮጀክት ቻርተር የተቀረጸ ሲሆን ይህም፤ ፕሮጀክቱን ለመምራት፣ ለማስተባበር፣ የባለድርሻ አካላትን ሃላፊነትና ተግባራት ለመለየት የሚዳስሱ ጉዳዮችን ያስቀምጣል።
 1. የፕሮጀክቱ ዓላማ
 • አይ.ሲ.ቲ. ቴክኖሎጂ መረጃን በቀላሉ ለማግኘት እንዲሁም ቴክኖሎጂን በአጠቃላይ ለመጠቀም በማስቻልና እውቀትን ቅርብ በማድረግ ለኢኮኖሚ እድገትና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ታሳቢ ተደርጒል። 
 • ፕሮጀክቱ ከፍተኛና የተለያየ አይነት ወጪ የሚጠይቀውን ልማዳዊና የመረጃ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ በማስወገድ ዘመናዊ አሰራርን የሚዘረጋ ይሆናል። ይህንን ማሳካት በተለያዩ ደረጃዎች በሚገኝ ፋይዳ የሚገለጽ ሲሆን እነዚህ መገለጫዎች የሚከተሉትነ ያካትታል፤
 • የሲቪል ሰርቪስ የሰው ሃይል መረጃን መዋሃድ፣
 • ለተሻሻለ የሰው ሃይል እቅድና አመራር ሁኔታ ማመቻቸት፣
 • ከእለታዊ ጉዳዮች ክንዋኔ ይልቅ በፖሊሲና ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው መረጃዎች ላይ ማተኮር ማስቻል፣
 • መረጃን በማግኘትና በማስገባት ሂደት ብቃት ማምጣት፣
 • የመረጃን ፍሰት ማቃለልና መከታተል ማስቻል፣
 • በአደጋ መረጃ ሲጠፋ/ሲበላሽ የሚውል የመጠባበቂያ መረጃ አያያዝ እድል መፍጠር።

 

 1. ኢ.ስ.ሚስ ፕሮጀክትን ስራ ላይ ማዋል
 • አዲሱ አሰራር በተመረጡ መስሪያ ቤቶች ላይ ከተሞከረና አስፈላጊ ማስተካከያ ከተደረገ በኋላ፤ከ200.6./07 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም የፌዴራልና የክልል ሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤቶች በስራ ላይ የማዋል ስራ ተጀምሯል።
 • በፕሮጀክቱ አዲስ አሰራር መረጃዎች እንደየባህሪያችው በተለያዩ ክፍሎች ተመድበዋል። እነሱም፤
 • የሰው ሀብት አስተዳደር ሞጁል፣
 • የመዋቅር ሞጁል፣
 • የኢንስፔክሽን ሞጁል፣
 • የአስተዳደር ፍ/ቤት ሞጁል፣
 • የአርካይቭና ሪከርድ ሞጁል ናቸው።

 

 1. ማጠቃለያ
 • የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኢ.ስ.ሚስ ፕሮጀክት አማካኝነት ላለፉት አምስት አመታት አዲሱን አሰራር በፌዴራልና ክልል መስሪያ ቤቶች በሚፈለገው ደረጃ ስራ ላይ መዋል እንዲችል ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ከዚህም አንፃር እንደተስተዋሉት ክፍተቶች ባህሪ የማስተካከያና የቴክኒክ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።
 • ይሁን እንጂ በታሰበው መጠን ወደ ስራ በመግባትና የተጠበቀውን ውጤት ከማግኘት ረገድ ክፍተቶች እንዳሉ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተገኘው ግብረ መልስ ያሳያል። እነዚህን ክፍተቶች በመለየትና እንደየባህሪያቸው እልባት በመስጠት ሂደት ያለፉት አመታት የፕሮጀክቱ ዋና የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በቀጣይም ተገቢ የሆነው ድጋፍ በማድረግ በየጊዜው የሚታዩ ክፍተቶችን ለመዝጋትና አዲሱ አሰራር በሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተገቢው ደረጃ ስራ ላይ እንዲውል ፕሮጀክቱ ድጋፉን የሚቀጥል ይሆናል።
 • ዘመናዊውን አሰራር በመላው ሃገሪቱ ከመዘርጋት ጎን ለጎን፤ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደረጃ ለዘማናት ሲከማቹ የኖሩ አጠቃላይ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሰራተኛ ሰነዶች ወደ ዲጂታል አያያዝ የማስገባት ስራ የተጀመረ ሲሆን እስካሁንም ከፍተኛ መጠን ያለው ሰነድ በዚህ መልክ መገልበጥ ተችሏል። ይሁን እንጂ አሁንም ከፍተኛ መጠን ላለው የሰራተኛ ሰነድ በድጂታል አሰራር የማስቀመጥ ስራ የቀረ በመሆኑ ይህን ቀሪ የሰነድ ክምችት ወደ አዲሱ አያያዝ ስርዓት የማስገባት ስራ በእቅድ ተይዞ ይገኛል። ለዚህም የውጭ ባለሙያን በመጠቀም ስራው በፍጥነት የሚጠናቀቅበትን ሁኔታ በመመቻቸት ላይ ይገኛል። የዚህ ተግባር መጠናቀቅ በጡረታ ዘመናቸው አበል ለማግኘት የሚከሰተውን ውጣ ውረድ ጨምሮ ብዙ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን ብቃትና ውጤታማነትን የሚላብስበት ሁኔታ እንደሚያመቻች ይታመናል።   

 

Hits: 1235

የውይይት መድረክ

የክስተቶች ካላንደር

JEvents - Legend Module

በቅርቡ የሚደረጉ ክስተቶች

No events

JEvents - Custom Module