







አዳዲስ ዜናዎች









የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄደ
*****************************************************
አዲስ አበባ፣ነሃሴ 25/2014 ዓ.ም.
በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ አጠቃላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ የውይይቱ መነሻም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር በሆኑት በዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ቀርቧል፡፡
በውይይቱም ለአገረ መንግስት ግንባታው የማይተካ ሚና ያለው የመንግስት ሰራተኛው የሶሻል ሚዲያን ሲጠቀም የሚያገኛቸውን መረጃዎች እውነተኛነት ሳያረጋግጥ የሃሰተኛና የአሉባልታ ወሬዎችን በመስማትና በማስፋፋት አገርን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ አለመሆኑን ሊያስተውል እንደሚገባ በዋነኛነት ተነስቷል፡፡
በዚህም ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ኢትዮጰያ አገራችን አሁን ካሉባት ወቅታዊ ፈተናዎች በመውጣት ደህንነቷንና ብልጽግናዋን እንደምታረጋግጥ በማመንና ዛሬ እየገጠሙ ያሉና ነገ ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመገንዘብ በተሰማራበት የስራ ዘርፍ የሃላፊነት ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
“መንግስት ሰራተኛው ከሚናፈሱ የአሉባልታ ወሬዎች ራሱን በመጠበቅ በተሰማራበት የስራ ዘርፍ የሃላፊነት ግዴታውን ሊወጣና ለአገር አንድነትና ቀጣይነት ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡”
Hits: 3497
የውይይት መድረክ
የክስተቶች ካላንደር
JEvents - Legend Module
በቅርቡ የሚደረጉ ክስተቶች
No events |