ለተደራጀ ለውጥ መፋጠን የህዝብ ክንፉን ተሳትፎ ማጠናከር ይገባል ተባለ

ቢሾፍቱ ነሃሴ 10/2014 ዓ.ም.
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመንግስት ሰራተኞች የብቃት ማእቀፍ አዘገጃጀትና ትግበራ ዙሪያ ከተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ ምሁራኖችና ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ ማካሄድ ጀመረ፡፡ *****************************************************************************************
ኮሚሽኑ ከUNDP ጋር በመተባበር በመንግስት ሠራተኞች የብቃት ማዕቀፍ አዘገጃጀትና ትግበራ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ (ETQF) ጋር አጣጥሞ የሠለጠነ የሠው ሃይል ፍላጎትና አቅርቦት ለመምራት ከተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ምሁራኖች ጋር በመሆን በክቡር ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና ምክትል ኮሚሽነሮች አወያይነት የጋራ ምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በምክክር መድረኩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ከአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ፣ ከኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የብቃት ማዕቀፍ አዘገጃጀትና ትግበራ፣ በብቃት ምዘና መሳሪያዎች አዘገጃጀትና ትግበራ እንዲሁም በምዘና መሳሪያዎች አዘገጃጀትና ትግበራ ስርዓትና በምዘና መረጃዎች ስራ አመራር ስርዓት ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በመጡ ባለሙያዎች ጽሁፎች ቀርበዋል፡፡
መድረኩ አንድ ቀን የሚቀጥል ሲሆን፣ በቀጣይነትም ኮሚሽኑ ያዘጋጀው የመንግስት ሠራተኞች የብቃት ማዕቀፍ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡
Hits: 700